ታሪካዊ የኤሌክትሪክ አውቶቡስ ጉዞ ከናይሮቢ እስከ አዲስ አበባ!
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ይፋ እንዳደረገው፣ በቢኬጂ (BKG) የተገጣጠሙ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ አውቶቡሶች ከናይሮቢ እስከ አዲስ አበባ ታሪካዊ ድንበር ተሻጋሪ ጉዞ እያደረጉ ይገኛሉ። እነዚህ አውቶቡሶች በኬንያ ናይሮቢ የተካሄደውን የ«Nordic-Africa EV Summit» ጉባኤ ተሳታፊዎችን ይዘው ሞያሌን በማቋረጥ ወደ አዲስ አበባ እየተጓዙ ሲሆን፣ ተልዕኳቸውን አጠናቀው ሲመለሱም ተመሳሳይ ጉዞ እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
ይህ የምሥራቅ አፍሪካን የኤሌክትሪክ ተንቀሳቃሽነት ምዕራፍ የሚያሳየው ታሪካዊ ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን ከአዲስ አበባ 560 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ያቤሎ ከተማ የኤሌክትሪክ ቻርጅ ማዕከል ሆና እየገለገለች ይገኛል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እንደገለጸው፣ ይህንን ታሪካዊ ስኬት እውን ለማድረግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ቢኬጂ (BKG)፣ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ (AATB)፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የፌዴራልና የክልል ፖሊስ ተቋማት የተቀናጀ ሚና ተጫውተዋል።
#afromekina
Loading content...
