ከጎሮ አደባባይ - ኮዬ ፈጬ የሚወስደው መንገድ በከፊል ለትራፊክ ዝግ ይደረጋል ተብሏል።
ትላንት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ከኮዬ ወደ ጎሮ አደባባይ የሚወስደው አስፋልት መንገድ ተቆርጦ እየተሰራ መሆኑን ገልጾ ነበር።
በሥፍራው ላይ እየተካሄደ ባለው የግንባታ ሥራ ምክንያት ከነገ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ እሁድ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ፤ ከጎሮ አደባባይ - ኮዬ ፈጬ የሚወስደው መንገድ በከፊል ለትራፊክ ዝግ ይደረጋል ብሏል።
በዚህም ፦
👉 ከኮዬ ፈጬ ወደ ጎሮ አደባባይ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች በቡልቡላ በኩል - ቦሌ ኤርፖርት - ጎሮ አደባባይ የሚወስደውን አዲሱን መንገድ እንዲጠቀሙ፤
👉 ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ ፈጬ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች፣ የትራፊክ መጨናነቅ ሁኔታን ለመቀነስና ጊዜ ለመቆጠብ፤ ከጎሮ - በቦሌ ኤርፖርት አዲሱ መንገድ በመጠቀም በቡልቡላ በኩል ወደ ኮዬ አደባባይ መጓዝ እንደሚችሉ ተገልጿል።
#afromekina
Loading content...
