ተሽከርካሪዎች የለጠፉትን ጥቁር ስቲከር እንዲያነሱ የጋምቤላ ክልል ፖሊስ አሳሰበ
የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከተለዩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ወይም VIP ተሽከርካሪዎች በስተቀር በጋምቤላ ከተማ ፣ በሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች በሚገኙ ማናቸውም ተሽከርካሪዎች መስታወት ላይ የተደረጉ ጥቁር ስትኬሮች ሙሉ በሙሉ እንዲነቀሉ ማሳሰቢያ ሰጠ።
ኮሚሽኑ በክልሉ ሰላምና ጸጥታን ለማረጋገጥ እንዲሁም የጸጥታ ቁጥጥር ሥራዎችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በክልሉ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ፣ የግል ፣ የንግድ ፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የፕሮጀክት ተሽከርካሪዎች በሙሉ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።
ይህ የጸጥታ መመሪያ በሁሉም የክልሉ አወቃቀሮች በጥብቅ የሚተገበር ሲሆን፤ መመሪያውን ጥሰው በተሽከርካሪዎቻቸው መስታወት ላይ ጥቁር ስትኬር ይዘው በተገኙ አካላት ላይ ኮሚሽኑ ጥብቅ ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑንም አስገንዝቧል።
የመንግሥት አመራሮች፣ ሕብረተሰቡና የድርጅት ኃላፊዎች ለሕግ ማስከበር ሥራው መሳካት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አስተላልፏል።
ምስል በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ(AI) የበለፀገ
#afromekina
Loading content...
