ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊያን የሚገጣጠሙ (CKD) የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች
የMJ Motors ኩባንያን የስራ እንቅስቃሴ በጎበኘንበት ወቅት፣ በኢትዮጵያ የሚገጣጠሙ የኤሌክትሪክ መኪኖች የሃገር ውስጥ እሴት ጭማሪ (Value Addition) በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መሆኑን በተግባር ተመልክተናል።
ስራውን ተስፋ ሰጪ የሚያደርገው 95% የሚሆነው ተግባር የሚከናወነው በኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎችና መሀንዲሶች መሆኑ ለሀገራችን የቴክኖሎጂ ሽግግር (Technology Transfer) ትልቅ መሠረት የሚጥል መሆኑ ነው። በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ማደግ፣ ምርቱን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ለማቅረብ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር እንደሆነ ከምርት ሂደታቸው እና ከማምረቻ ወጫቸው ተረደተናል::
መንግስት ሰፊ የስራ ዕድል ለሚፈጥሩ ፣ ቴክኖሎጂ ለሚያሸጋግሩ ፣ የውጭ ምንዛሬን በመቆጠብ እና አረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት ከፍተኛ ሚና ያላቸውን ኩባንያዎች መደገፉን አጠናክሮ ይቀጥላል።
#afromekina
Loading content...
