የነዳጅ ድጎማ ወጪ ከታቀደው በ172 በመቶ ብልጫ አሳየ!
የኢትዮጵያ መንግስት ለ2018 የበጀት ዓመት ለነዳጅ ድጎማ መድቦት ከነበረው 100 ቢሊዮን ብር እጅግ በላቀ ሁኔታ፣ 272 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉ ተገልጿል።
ይህ በዕቅዱ ላይ የታየው የ172 በመቶ ብልጫ፣ በባህረ ሰላጤዉ እየተባባሰ ከመጣው ውጥረት ጋር ተዳምሮ አገሪቱ የጀመረችውን አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ በማህበራዊ ገጻቸው ባጋሩት መረጃ መሰረት፣ ይህ የወጪ ጭማሪ የታየው መንግስት የነዳጅ ድጎማን ደረጃ በደረጃ ለማንሳትና የገበያ መር ኢኮኖሚ ለመገንባት ቃል ገብቶ ወደ ተግባር በገባ ጥቂት ወራት ውስጥ ነው።
ለነዳጅ ድጎማ የተያዘው በጀት ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት 0.6 በመቶ ወይም 100 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ወጪው ወደ 272 ቢሊዮን ብር አሻቅቧል።
#afromekina
Loading content...
