በአንድ ወር ወስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ
ነጭ ናፍጣ በሊትር 180.46 ብር ገብቷል። ቤንዚንም በሊትር 167.50 ብር ሆኗል።
ከሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉን ማደያዎች ገለጹ።
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ደብዳቤ፣ የዓለም የነዳጅ ዋጋን መሰረት በማድረግ ከሚያዚያ 23 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ መደረጉን ያስረዳል።
በደብዳቤው በተገለጸው መሰረት በሊትር፦
- ነጭ ናፍጣ 180.46 ብር
- ቤንዚን 167.50 ብር
- ኬሮሲን 320.66 ብር
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ 170.62 ብር
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ 167.37 ብር
- የአውሮፕላን ነዳጅ 319.76 ብር ሆኗል።
በነዳጅ ምርቶች ላይ ከአንድ ወር በፊት የዋጋ ጭማሪ ተደርጎ ነበር።
#afromekina
Loading content...
