ነዳጅ ከዛሬ ህዳር 15 ጀምሮ ለግል ተሽከርካሪዎችም መሰራጨት እንደሚጀምር ተገልጿል።
በመቐለ ከተማ ለቀናት ለመንግሥታዊ አገልግሎቶች ብቻ ሲቀርብ የቆየው ነዳጅ ከዛሬ ህዳር 15 ጀምሮ ለግል ተሽከርካሪዎችም መሰራጨት እንደሚጀምር ተገልጿል።
የትግራይ ባለአደራ አስተዳደር ባወጣው መረጃ፣ ነዳጅ ወደ መቐለ ከገባ ከሳምንት በላይ መቆየቱንና በዚህ ጊዜ ውስጥ ለመንግሥታዊ አገልግሎቶች ብቻ ሲውል መቆየቱን አስታውቋል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ - መቐለ ዘጋቢዎች በከተማዋ ወደሚገኙ ነዳጅ ማደያዎች በመዘዋወር ባደረጉት ምልከታ፣ ነዳጅ ለመንግሥታዊ አገልግሎቶች ብቻ እየተሰራጨ መሆኑን ተረድቷል።
በትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር የኢኮኖሚና መልሶ ግንባታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ቴድሮስ ኣረጋይ ከንግድና መጓጓዣ ዘርፍ አመራሮች ጋር ዛሬ ባካሄዱት ውይይት፣ ከህዳር 15 ጀምሮ ነዳጅ ለግል ተሽከርካሪዎች እንዲሰራጭ መወሰኑ ተገልጿል።
ሆኖም ከመቐለ ከተማ ውጭ ባሉ ሌሎች የትግራይ ከተሞች የነዳጅ አቅርቦቱ መቼ እንደሚጀምር የሚያመለክት መረጃ እስካሁን አልተገኘም።
የመቐለ ዘጋቢዎቻችን በክልሉ ነዳጅ አሁንም ድረስ በጥቁር ገበያ በየመንገድ ዳሩ እንደሚሸጥ ፤ እስከ 950 ደርሶ የሚያውቅበት ጊዜ እንደነበር አሁን ነዳጅ ገባ ከተባለ ወዲህ 2 ሊትሩ በጥቁር ገበያ እስከ 530 ብር እንደሚሸጥ ገልጸዋል።
ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በትግራይ ክልል በተከሰተው ጦርነት ምክንያት የነዳጅ አቅርቦት ከፍተኛ ችግር ገጥሞት ቆይቷል። በዚህም ነዳጅ ከመደበኛ ማደያዎች ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ሆኖ በግለሰቦች በጀሪካን እና ውሃ ማሸጊካ ፕላስቲክ በመንገድ ዳር እየተሸጠ ይገኛል።
#afromekina
Loading content...
