የውጭ ባለሀብቶች እና ተቋማት ነዳጅ እንዲያስገቡ ተፈቀደ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሃገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ስርዓት ላይ እየደረሰ ያለውን ጫና ለማቃለል በማለም፤ ኤምባሲዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና በዉጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሀብቶች በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ ነዳጅ እንዲያስገቡ የሚፈቅድ አዲስ መመሪያ ተግባራዊ አድርጓል።
ባለፈዉ ሳምንት ይፋ የሆነዉ ይህ መመሪያ፤ እውቅና የተሰጣቸው ተቋማት የተጣራ የነዳጅ ምርቶችን በፍራንኮ ቫሉታ ስርዓት እንዲያስገቡ የሚፈቅድ ሲሆን፣ ይህም ከሀገር ውስጥ የባንክ ስርዓት ምንም ዓይነት የውጭ ምንዛሬ ሳይጠይቁ የራሳቸውን ፍላጎት እንዲሸፍኑ የሚያስችል ነው።
ይሁን እንጂ አዲሱ አሰራር አጠቃላይ የነዳጅ ገበያውን ለግል ነጋዴዎች ክፍት የሚያደርግ ባለመሆኑ፣ በዚህ መንገድ የገባ ነዳጅ ለሕዝብ ሊሸጥ፣ ለሶስተኛ ወገን ሊተላለፍ ወይም በተለመደው የሀገር ውስጥ የንግድ ነዳጅ አቅርቦት ላይ ሊቀላቀል እንደማይችል በጥብቅ መከልከሉን የዘገበው ካፒታል ጋዜጣ ነዉ።
#afromekina
