የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት (EEU) በሀገር አቀፍ ደረጃ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጂንግ መረቡን ለማስፋት በመጀመሪያው ምዕራፍ 40 የሕዝብ ቻርጂንግ ጣቢያዎችን እየገነባ መሆኑ ተገልጿል። ከነዚህም ውስጥ 32ቱ በአዲስ አበባ፣ ቀሪዎቹ 8ቱ ደግሞ በዋና ዋና የክልል ከተሞች ይገነባሉ።
በቅርቡ በቂሊንጦ አካባቢ በአንድ ጊዜ 24 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል ፈጣን ቻርጂንግ ጣቢያ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር ሥራ ጀምሯል። በኮተቤም 170 ሚሊዮን ብር የወጣበት ጣቢያ ተመርቋል። ኢትዮ ቴሌኮምም በአዲስ አበባና በአዳማ ጨምሮ ዘጠኝ ጣቢያዎችን እያንቀሳቀሰ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኃላፊዎች እንደገለጹት ከ140 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ቢገቡም የቻርጂንግ መሠረተ ልማቱ ገና ከፍላጎቱ ጋር አልተመጣጠነም። አዳዲሶቹ ጣቢያዎች ይህን ክፍተት ለማጥበብ ታቅደዋል።
ለአፍሮመኪና ተጠቃሚዎች፡ የኤሌክትሪክ መኪና ለመግዛት ሲያስቡ በመኖሪያና በሥራ ቦታዎ አቅራቢያ ያሉ ቻርጂንግ ጣቢያዎችን አስቀድመው ይመልከቱ።
