ኢትዮጵያ የባቡር ትራንስፖርት ዘርፏን የሚያዘምኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ይፋ አደረገች
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከህንዱ «ፊዛ ኤሊክሰር ኢንፍራስትራክቸር» ኩባንያ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ታሪካዊ የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።
የዚሁ ስምምነት ዋና ዓላማ በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘውን ወርክሾፕ በማስፋፋት፤ የባቡር ጥገና፣ የመለዋወጫ እቃዎችና የባቡር አካላት ማምረቻ ማዕከል አድርጎ መገንባት ነው።
በተጨማሪም በቀን በሺዎች የሚቆጠሩ መንገደኞችን የሚያስተናግደውን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ለማሻሻል የሚያስችሉ ተግባራት ይከናወናሉ።
ከነዚህም መካከል፡-ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ ቲኬትአሰራርን መዘርጋት፣ተጨማሪ ባቡሮችን ወደ አገልግሎት ማገባት፣ እንዲሁም
የኤሌክትሪክ፣ የሲግናል እና የመገናኛ ስራዎችን ማዘመን ይጠቀሳሉ።
ይህ ስምምነት የሀገሪቱን የባቡር ትራንስፖርት ዘርፍ ከማዘመኑ ባሻገር፣ የሀገር ውስጥ አቅምን በማሳደግ ለዘላቂ የልማትና የንግድ ዕድሎች ትልቅ በር ይከፍታል ተብሎ ተጠብቋል።
ምስል በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ(AI) የተሰራ
#afromekina
Loading content...
