ኢትዮጵያ በካሉብ ጋዝ መስክ ሁለተኛ ምዕራፍ የተፈጥሮ ጋዝ ማቀነባበሪያ ግንባታ ልታስጀምር ነው
⛽️ ጂሲኤል እና ጁሮንግ የተባሉ ሁለት የቻይና ኩባንያዎች በኦጋዴን ተፋሰስ በሚገኘው የካሉብ ጋዝ መስክ የ2ተኛ ምዕራፍ የተፈጥሮ ጋዝ ግንባታና ማቀነባበር ስምምነት ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር መፈራረማቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ዝርዝሮች ነጥቦች፦
የተደረገው ስምምነት፦ ቀደም ሲል የነበረውን ትብብር ወደ ተግባር የሚቀይር ሲሆን፤ የማቀነባበሪያ ተቋማት ግንባታንና የሎጂስቲክስ መሰረተ ልማቶችን ያካትታል።
የመጀመሪያው ምዕራፍ፦ በጥቅምት 2018 ዓ.ም. ተመርቆ በቀን 200 ሺህ ሜትር ኩብ ጋዝ የሚያቀነባብረው የመጀመሪያው ምዕራፍ ለሀገር ውስጥ አቅርቦት ውሏል።
የሁለተኛው ምዕራፍ አላማ፦ ምርትን በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመር ለውጭ ገበያ ማቅረብ ነው።
የማዕድን ሚኒስቴር ግንባታው በፍጥነት እንዲጀምር ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፤ የውሉ የገንዘብ መጠንና የሚያልቅበት ጊዜ አለመገለጹን ዘገባው አመላክቷል።
#afromekina
Loading content...
