ኢትዮጵያ አዲስ የባቡር ነዳጅ ማጓጓዣ አማራጭ ልታገኝ ነው
በጅቡቲ እየተገነባ ያለው ግዙፉ ፕሮጀክት!
በጅቡቲ የዶራሌህ ሁለገብ ወደብ አዲስ የነዳጅ ማከማቻ ታንኮች ግንባታ በስፋት እየተካሄደ ነው። አፍሪካን ተርሚናል ኤንድሎጂስቲክስ ሰርቪስ እውን እያደረገው ያለው ይህ ፕሮጀክት፣ ነዳጅን በቀጥታ ከማከማቻው ወደ ባቡር በመጫን ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዝ የሚያስችል ታሪካዊ ዕቅድ ይዟል።
ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በየብስ ትራንስፖርት ላይ ብቻ ጥገኛ የሆነውን የነዳጅ ኮሪደር ከጫና ነፃ ያወጣዋል ተብሎ ይጠበቃል።
አሁን ላይ በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ የነዳጅ ቦቴ መኪኖች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚመላለሱ ሲሆን፣ አዲሱ የባቡር ማጓጓዣ ሥርዓት ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማድረስ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
#afromekina
Loading content...
