በኢትዮጵያና ጅቡቲ የትራንስፖርት መስመር
የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ኔትወርክ ሊዘረጋ ነው
በኢትዮጵያና በጅቡቲ ኮሪደር ላይ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ መሙያ ኔትወርክ ለመዘርጋት ከሶስት ታዋቂ የውጭ ኩባንያዎች ጋር የጋራ ኢንቨስትመንት ስምምነት መፈጸሙን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው እንደገለጹት፤ ከአዲስ አበባ እስከ ጅቡቲ ባለው የትራንስፖርት መስመር ላይ ይህንን አውታር ለመዘርጋት ከቻይና ሮድ ኤንድ ብሪጅ ኮርፖሬሽን፣ ከቤጂንግ ፎርኤቨር ቴክኖሎጂ ሊሚትድ እና ከሁዋዌ ቴክኖሎጂስ ጋር ስምምነት ተደርጓል።
ይህ የትብብር ማዕቀፍ ጣቢያዎቹ የሚገነቡባቸውን አካባቢዎች በመለየት፣ የቴክኒክ ሞዴሎችን በማውጣት እና የቻርጅ ጣቢያዎችን በኮሪደሩ ላይ በማቀናጀት ተደራሽነታቸውን ለማስፋት ያስችላል ተብሏል።
ይህ ታሪካዊ ፕሮጀክት አረንጓዴ የትራንስፖርት ሥርዓትን በማስተዋወቅ ለነዳጅ ግዢ የሚወጣውን ውድ የውጭ ምንዛሪ በእጅጉ ለመቀነስ፣ የአየር ንብረት ብክለትን ለመከላከል እና የታዳሽ ኃይል አጠቃቀምን ለማሳደግ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተገልጿል።
ከዚህም ባለፈ በሂደቱ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር፣ የባለሙያዎች አቅም እንዲያድግ እና በርካታ የሥራ ዕድሎች እንዲፈጠሩ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተመላክቷል።
#afromekina
Loading content...
