የኤሌክትሪክ መኪኖች ሽያጭ አዲስ ሪከርድ ሰበረ
በሃምሌ 2026 ብቻ 1.85 ሚሊዮን የኤሌክትሪክ መኪኖች በመሸጥ ዓለም አቀፍ የሽያጭ እድገት ማስመዝገብ ችሏል።
በአውሮፓ የመንግስት ድጎማዎች መታደስ ሽያጩን በ33 በመቶ ከፍ ሲያደርገው፣ በቀቀሩት የዓለም ክፍሎች ደግሞ የ97 በመቶ ከፍተኛ ጭማሪ ታይቷል። ከጥር እስከ ሃምሌ ባሉት ወራት ብቻ በአጠቃላይ 11.5 ሚሊዮን መኪኖች ተሽጠዋል።
በቻይና የሀገር ውስጥ ፍላጎት በመቀነሱ የሽያጭ መጠኑ በ5 በመቶ የቀነሰ ሲሆን፣ አምራቾች ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ መላክ ጀምረዋል።
በአሜሪካም የመንግስት የታክስ ማቃለያ በመነሳቱ ሽያጩ በ27 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።
ሆኖም ዓለም አቀፉ የኃይል ኤጀንሲ (IEA) በ2026 ከጠቅላላው የዓለም የመኪና ሽያጭ ውስጥ የኤሌክትሪክ መኪኖች ድርሻ 29 በመቶ ይደርሳል ብሎ ይጠብቃል።
#afromekina
Loading content...
