ግብፅ በሜዲትራኒያን ባሕር 5.7 ቢሊዮን ኩብ ሜትር የያዘ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት አገኘች
🇪🇬 ግብፅ በሜዲትራኒያን ባሕር ባካሄደችው የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ተስፋ ሰጪ ውጤት ማግኘቷንና በፍጥነት ምርት ማውጣት ለመጀመር ማቀዷን የሀገሪቱ የፔትሮሊየም እና የማዕድን ሀብት ሚኒስቴር አስታውቋል።
ዋና ዋና ዝርዝሮች፦
✔️የጋዝ ክምችት፦ 5.7 ቢሊዮን ኩብ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ ይዟል ተብሎ የተገመተ ሲሆን ጥቅም ላይ ሊውል የሚችለውን የተጣራ መጠን ለመወሰን ጥናቶች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።
✔️አዲስ የማስተላለፋያ መስመር ፦ የጋዝ ማውጣት ሂደቱን ለማፋጠን የጋዝ ጉድጓዱን ከነባር የመሠረተ-ልማት አውታር ጋር የሚያገናኝ 22 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ታቅዷል።
✔️ተጨማሪ የፍለጋ ሥራዎች፦ እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ ከሆነ የተሻሻሉ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎች እና ያልተከፈሉ ውዝፍ ክፍያዎች ለአጋሮች መከፈላቸው ተጨማሪ የፍለጋ ሥራዎችን ለማካሄድ መነቃቃትን ፈጥሯል።
#afromekina
Loading content...
