ዶዶይ (Dodai) የ 7 ሚሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት ፈንድ አገኘ።
በኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ሞተር ሳይክሎችን በማምረት ላይ የሚገኘው ዶዶይ (Dodai) በቅርቡ የ 7 ሚሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት ፈንድ ከጃፓን ባለሀብቶች አግኝቷል።
በጃፓናዊው ታይጂ ካኖ የሚመራው ይህ ኩባንያ፣ የተገኘውን ካፒታል በአብዛኛው የባትሪ ቅየራ (Battery Swapping) ጣቢያዎችን ለመገንባት እና የሶፍትዌር አቅምን ለማሳደግ እንደሚጠቀምበት ገልጿል።
ዶዳይ በቀጣይ የባትሪ ቅየራን ወደ አገልግሎት በማስገባት አሁን ካለው የመሸጫ ዋጋ ከ40 እስከ 50 በመቶ ለመቀነስ እና በቀጣይ 5 ዓመታት ውስጥ የዚህ ተጠቃሚ የሆኑ 50,000 ተጠቃሚዎችን ለማፍራት አቅዷል።
ይህ አገልግሎትም ባትሪን ቻርጅ ለማድረግ ከ4-6 ሰዓታት ከመጠበቅ ይልቅ፣ በአጭር ደቂቃ ውስጥ ያለቀበትን ባትሪ አውጥቶ ሙሉ በሙሉ ቻርጅ በተደረገ ባትሪ ለመቀየር የሚያስችል ነው ተብሏል።
ለዚህም እያንዳንዱ ባትሪ በውስጡ ባለው ሴንሰር አማካኝነት የጤንነት ሁኔታው ክትትል የሚደረግበት ሲሆን ተጠቃሚዎች ለቅየራ አገልግሎቱ የሚከፍሉበት የዲጂታል የክፍያ ሥርዓትም አለው።
ኩባንያው በአሁኑ ወቅት የባትሪ ቅየራ ጣቢያዎችን በአዲስ አበባ ውስጥ ለማስፋፋት በሂደት ላይ ይገኛል።
ሊቲየም-አዮን (Lithium-ion) ባትሪ የሚጠቀሙት እነዚህ ሞተሮች በሙሉ ቻርጅ ከ 120 እስከ 150 ኪሎ ሜትር እንደሚሄዱ ድርጅቱ ይገልጻል።
ኩባንያው ምርት ከጀመረበት ባለፉት 18 ወራት ውስጥ በሀገር ውስጥ የተገጣጠሙ ከ1,500 በላይ የኤሌክትሪክ ሞተሮችን ለገበያ ማቅረቡም ተነግሯል። አሁን በገቢያ ላይ 150 እስከ 200 ሺ ብር እየተሸጡ ይገኛሉ።
#afromekina
Loading content...
