1.6 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣውን ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ አክሲዮን ሽያጭ ጀመረ
ናይጄሪያዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ የ4.1 ቢሊዮን የነዳጅ ማጣሪያ አክሲዮኖችን እያንዳንዳቸውን በ0.40 ዶላር ለሽያጭ በማቅረብ በአፍሪካ እስካሁን ትልቁን የአክሲዮን ሽያጭ ጀምረዋል። የመጀመሪያው የአክሲዮን ሽያጩ በዛሬው ዕለት የተከፈተ ሲሆን ጥቅምት 3 ይዘጋል።
💰 አክሲዮኖቹ ሙሉ በሙሉ ከተሸጡ ሽያጩ 1.6 ቢሊዮን ዶላር ይሰበስባል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የፍላጎት መብዛት አጋጥሞ ተጨማሪ አክሲዮኖችን የመሸጥ መብት ሥራ ላይ ከዋለ ገቢው እስከ 2.1 ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል።
🇳🇬 ይህ የአክሲዮን ሽያጭ ለግለሰብ ባለሀብቶች በማጣሪያው ውስጥ አክሲዮን የመግዛት ዕድል የሚሰጥ ሲሆን፣ ዳንጎቴ ገንዘቡን ለማጣሪያው ማስፋፊያ ዕቅዶች ለማዋል ይፈልጋሉ።
#afromekina
Loading content...
