የአቃቂ ድልድይ ግንባታ 95 በመቶ ተጠናቋል ተባለ
የዚህ ድልድይ ግንባታ መጓተት በአከባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ሲቀርብበት ቁይቷል።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፣ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል አካባቢ እየተገነባ የሚገኘው የአቃቂ ወንዝ መሻገሪያ ድልድይ ግንባታ 95 በመቶ መድረሱን የከተማዋ መንገዶች ባለስልጣን አሳውቋል።
ባለስልጣኑ በመረጃው ድልድዩ መቼ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን አልገለፀም ።
62 ሜትር ርዝመትና 25 ሜትር ስፋት ያለው ድልድዩ የማጠናቀቂያ ሥራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፣ 220 ሜትር የሚረዝመው የመቃረቢያ መንገድ ግንባታም በመፋጠን ላይ ይገኛል ተብሏል።
የፕሮጀክቱን ግንባታ ሥራ ብሪጅ ኮንስትራክሽን የተባለ ሀገር በቀል ተቋራጭ እያከናወነ ሲሆን፣ የማማከርና ቁጥጥር ሥራውን ኔት ኮንሰልቲንግ እየተከታተለ ይገኛል።
ድልድዩ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በቃሊቲ፣ አቃቂና ቱሉ ዲምቱ አቅጣጫዎች ያለውን የትራፊክ ፍሰት ከማቀላጠፉም በላይ ለአካባቢው ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ይጠበቃ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በማህበራዊ ትስስ ገጹ አስነብቧል ።
#afromekina
Loading content...
