የቻይና የጥቅምት ወር የነዳጅ ግዥ ከመጋቢት ወዲህ ከፍተኛው ደረጃ ላይ ደረሰ
የኢራን ጦርነት በመካከለኛው ምስራቅ የነዳጅ አቅርቦት ላይ መስተጓጎል የፈጠረ ቢሆንም፣ የቻይና የጥቅምት ወር የጥሬ ነዳጅ ግዥ ከያዝነው ዓመት መጋቢት ወር ወዲህ ከፍተኛው ደረጃ ላይ መድረሱን ይፋዊ መረጃዎች አመላክተዋል።
የዓለማችን ትልቋ የነዳጅ ገዢ የሆነችው ቻይና በጥቅምት ወር ውስጥ 41.94 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ጥሬ ነዳጅ ማስገባቷን የሀገሪቱ የጉምሩክ መረጃ ያሳያል። ይህም በቀን ከሚገባው የነዳጅ መጠን አንጻር መስከረም ወር ጋር ሲነጻጸር የ9.4 በመቶ እድገት አሳይቷል።
ሆኖም የጥቅምት ወር የነዳጅ ግዥው ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ13.3 በመቶ ቅናሽ ያሳየ ሲሆን፣ በዓመቱ የመጀመሪያዎቹ 10 ወራት የገባው ጠቅላላ የነዳጅ መጠን 399.9 ሚሊዮን ቶን መድረሱ ታውቋል። ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸርም በ15.1 በመቶ ዝቅ ማለቱ ተገልጿል።
#afromekina
Loading content...
