ቻይና በኤሌክትሪክ እና በነዳጅ የሚሰራውን አውሮፕላን በስኬት አበረረች
ቻይና በአየር ትራንስፖርት ቴክኖሎጂ ዘርፍ ዓለምን የሚያስደንቅ ታላቅ እርምጃ በመውሰድ በዓለም የመጀመሪያው የሆነውንና በኤሌክትሪክ እና በነዳጅ ኃይል የሚሰራ አነስተኛ የመንገደኞች አውሮፕላን የሙከራ በረራ በስኬት አከናውናለች።
ይህ አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራውን በኤሌክትሪክ እና በነዳጅ ጥምረት ያከናወነ ሲሆን ይህም የዓለም አቀፉን የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል።
ይህ እጅግ ዘመናዊ አውሮፕላን ሦስት ቶን የሚመዝን የመነሻ ክብደት ያለው ሲሆን እስከ 600 ኪሎ ግራም ጭነት የመሸከም ከፍተኛ አቅም አለው።
#afromekina
Loading content...
