ቡርኪና ፋሶ የነዳጅ አቅርቦትን ለማረጋጋት የናፍጣ ዋጋን በሊትር ከ1.18 ወደ 1.32 ዶላር አሳደገች
🇧🇫 የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው ይህ ውሳኔ፤ የነዳጅ አቅርቦትን ለማረጋጋት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
የዋጋ ጭማሪው ምክንያቶች፦
1️⃣ መንግሥት ነዳጅ ላይ ድጎማ በማድረግ ዋጋን ለማረጋጋት ቢጥርም፤ ወጪው ከሀገሪቱ አቅም በላይ እየሆነ መምጣቱን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ከፈረንጆቹ 2026 መግቢያ ጀምሮ እስካሁን ለድጎማ ከ105 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን እርምጃ ካልተወሰደ ይህ ቁጥር ከ238 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሊያልፍ እንደሚችል ተገልጿል።
2️⃣ የናፍጣ ዋጋ ውድ ከሆነባቸው ጎረቤት ሀገራት በርካታ ተሽከርካሪዎች ወደ ቡርኪና ፋሶ በመግባት ነዳጅ ይሞላሉ። አጓጓዦቹ ተጨማሪ ነዳጅ በበርሜል ጭነው የሚወጡ በመሆኑ፤ ለሀገሪቱ የነዳጅ እጥረትና አላስፈላጊ ፍጆታ ምክንያት ሆነዋል።
የሃይድሮካርቦን ዋጋዎች በይነ-ሚኒስቴር ኮሚቴ ሰብሳቢ አብዱል ሰላም ጋምፔኔ፤ ይህ ማስተካከያ በሸቀጦች ዋጋ ላይ ጭማሪ ማምጣት እንደሌለበት በመግለጽ፤ ነጋዴዎች አጋጣሚውን ተጠቅመው ዋጋ እንዳይከምሩ አሳስበዋል።
#afromekina
Loading content...
