አንጎላ በ2026 ለነዳጅ ድጎማ ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ልትወጣ እንደምትችል ተገለፀ
አንጎላ በ2026 ለነዳጅ ድጎማ 4 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ወጪ ልታወጣ እንደምትችል አንድ ከፍተኛ የፋይናንስ ባለሥልጣን ተናግረዋል ።
የገንዘብ መጠኑ ከዚህ በፊት መንግስት እቅድ ከያዘው የወጪ ግምት በእጥፍ የሚጠጋ ነው። ወጪው በመካከለኛው ምሥራቅ ከተባባሰው ግጭት ጋር ተያይዞ በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ መጨመሩን ተከትሎ የመጣ ነው።
መንግስት በዓለም ገበያ የሚጨምረው የነዳጅ ዋጋ ሸማቾች ላይ ሙሉ በሙሉ እንዳይጫን የሀገር ውስጥ የነዳጅ ዋጋ ላይ ድጎማ ያደርጋል ።
ይህ አሰራር ለመንግስት ተጨማሪ የበጀት ጫና በመፍጠሩ ከ2023 ጀምሮ መንግስት የነዳጅ ድጎማውን ቀስ በቀስ ለማንሳት እየሰራ ነው ።
#afromekina
Loading content...
