የአፍሪካ ኢነርጂ ባንክ በ5 ቢሊዮን
ዶላር ካፒታል በይፋ ተመሠረተ
የአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ (Afreximbank) እና የአፍሪካ የነዳጅ አምራቾች ድርጅት (APPO) በጋራ በመሆን 'የአፍሪካ ኢነርጂ ባንክ'ን በይፋ መሥረታቸውን አስታውቀዋል።
ባንኩ በ5 ቢሊዮን አሜሪካን ዶላር ካፒታል የተቋቋመ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም ዓለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት ከካርቦን እና ነዳጅ ነክ ፕሮጀክቶች ፋይናንስ ማውጣታቸውን ተከተሎ፣ በአህጉሪቱ የኢነርጂ ዘርፍ የተፈጠረውን ከፍተኛ የገንዘብ ክፍተት መሙላት ነው።
በተጨማሪም ባንኩ ዋና መሥሪያ ቤቱን በናይጄሪያ መዲና አቡጃ ማድረጉ የተገለጸ ሲሆን፣ የአፍሪካን የነዳጅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ እና የታዳሽ ኢነርጂ ሀብቶች በማልማት አህጉሪቱ በኢነርጂ ዘርፍ ራስዋን እንድትችልና የኤሌክትሪክ አቅርቦት እጥረትን እንድትቀርፍ ትልቅ ድጋፍ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
#afromekina
Loading content...
