የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ የወረቀት ትኬት ሊያስቀር ነው
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በ2019 ዓ.ም. ጀምሮ የወረቀት ትኬት አሰጣጡን ሙሉ ለሙሉ በማስቀረት የዲጂታል ስርዓት እንደሚዘረጋ አስታወቀ።
ይህ ዘመናዊ አሰራር ተገልጋዮች የዲጂታል ክፍያ ስርዓት እንዲጠቀሙ በማድረግ የተቀናጀ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ተገልጿል።
የድርጅቱ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደገፉ ገብረመድን እንደገለጹት፤ አሰራሩ ለህብረተሰቡ ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ትልቅ ሚና አለው።
ከተጠቀሰው ዓመት ጀምሮ ተሳፋሪዎች በወረቀት ትኬት ፋንታ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ብቻ ክፍያቸውን ፈጽመው ጉዞ ማድረግ እንደሚችሉ አሃዱ ሬዲዮ ዋና ሥራ አስፈጻሚውን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
#afromekina
Loading content...
