አዲስ አበባ 600 የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን ልታስገባ ነው
በኤሌክትሪክ የሚሰሩ 600 የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች እስከ መጋቢት 2019 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ ተፈራ ሞላ (ዶ/ር) ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ የአውቶቡሶቹ የግዥ ሂደት ተጠናቆ አሁን ላይ በምርት ሂደት ላይ ይገኛሉ። አዲስ የሚገቡት አውቶቡሶች ከዚህ ቀደም ሀገር ውስጥ ከሚገኙ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ጋር በመቀናጀት የከተማዋን የትራንስፖርት ስምሪት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል።
ይህ የትራንስፖርት አቅም ግንባታ ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን የኮፕ 32 (COP 32) ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በስኬት ለማካሄድ ያግዛል ያሉት ኃላፊው፤ የጉባኤውን ተሳታፊዎች ብዛት ታሳቢ በማድረግ በኤሌክትሪክና በተፈጥሮ ጋዝ የሚንቀሳቀሱ ተጨማሪ ተሽከርካሪዎችን ወደ ስርዓት የማስገባት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን የከተማ አስተዳደሩ ሀገር አቀፍ ዲዛይንን መሠረት ያደረገና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የተቀናጀ የትራንስፖርት ስምሪት ስርዓት እየዘረጋ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ለስርዓቱ ስኬታማነትም የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶችን የማበልጸግ እንዲሁም ለአሽከርካሪዎችና ተቆጣጠሪዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን የመስጠት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ለኮፕ 32 ጉባኤ የሚከናወኑ የትራንስፖርት ልማት ስራዎች ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ዘላቂ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ ለንግድ መቀላጠፍና ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ጠንካራ መሰረት ጥለው የሚያልፉ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።
#afromekina
Loading content...
