የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 5መቶ አዳዲስ የኤሌክትሪክ አዉቶብሶችን ሊያስገባ ነዉ
ከኢትዮ ኤፍኤም ጋር ቆይታ ያደረጉት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው፤የከተማዋን የትራንስፖርት ዘርፍ ወደ ቴክኖሎጂ ለማሸጋገር በተያዘዉ ዕቅድ 5መቶ አዳዲስ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን ለመግዛት በሂደት ላይ መሆኑን አስታውቋል።
በአሁኑ ወቅት 1መቶ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆን፤ እነዚህ ተሽከርካሪዎች በዘመናዊ ካሜራዎችና በጂፒኤስ የተገጠሙ በመሆናቸው ስምሪታቸውን ከመሃል ሆኖ ለመቆጣጠር አመቺ ሆነዋል ብለዋል።
ይህ የቴክኖሎጂ ሽግግር አውቶቡሶች ከተመደበላቸው መስመር እንዳይወጡና የአገልግሎት ጥራታቸው እንዲጠበቅ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ነው ተብሏል።
አውቶቡሶቹ በውስጣቸው ባላቸው ካሜራ አማካኝነት የአሽከርካሪዎችን ስነ-ምግባርና የተሳፋሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል አሰራር ተዘርግቶላቸዋል።
የቴክኖሎጂ አጠቃቀሙ በሰው ኃይል የሚደረገውን ቁጥጥር በማቀላጠፍና የህገ-ወጥ ድርጊቶችን ዕድል በማጥበብ ረገድ ትልቅ ለውጥ እያመጣ ነው።
አዲስ አበባ በኤሌክትሪክ ትራንስፖርት አጠቃቀም በአፍሪካ ግንባር ቀደም ከተማ ለመሆን በምታደርገው ጥረት እነዚህ አውቶቡሶች እንደ ትልቅ ምሰሶ እንደሚቆጠሩ ተመልክቷል።
#afromekina
Loading content...
