አዲስ የመንገድ ግብር ሊጣል ነው
በመንግስት በተሰሩ መንገዶች ላይ ለሚነዱ መኪኖች አዲስ ዓመታዊ የመንገድ ግብር ሊጀመር መሆኑ ተሰማ።
ይህ ግብር ከመኪና ዓመታዊ ምርመራ (ቦሎ) ጋር አብሮ የሚሰበሰብ ሲሆን፤ ክፍያውም እንደ መኪናው ዓይነት እና እንደሚያወጣው የካርቦን ጭስ መጠን ይወሰናል።
በዚህም መሰረት ብዙ ጭስ የሚለቁ አሮጌ መኪኖች ከፍተኛ ግብር ሲከፍሉ፣ አዳዲሶቹ ደግሞ ዝቅተኛ ግብር ይከፍላሉ ተብሏል።
እንደ ኢትዮ ኤፍ ኤም መረጃ፣ ይህ አሰራር በሌሎች አገሮችም የሚሰራበት ሲሆን መንግሥት የመንገድ ጥገና ሥራዎችን ለመሥራት ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያገኝ ይረዳል።
ግብሩ በከተሞችና በክልሎች ጭምር ስለሚሰበሰብ የአካባቢ መስተዳድሮች የራሳቸውን በጀት እንዲያጠናክሩና በፌዴራል መንግሥት ላይ የሚኖረውን የገንዘብ ጫና እንዲቀንሰው ታቅዷል።
ይህ አዲስ የታክስ ሃሳብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተዘጋጅቶ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀርቧል።
#afromekina
Loading content...
