የኤሌክትሪክ መኪኖችን ታሪክ የሚቀይር አዲስ የቻይና ግኝት
የቻይናው የቅንጡ መኪኖች አምራች Hongqi ከCNET ጋር በመተባበር የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙላት ፍጥነትን በከፍተኛ ደረጃ ያሻሻለ አዲስ ቴክኖሎጂ አስተዋወቀ። ይህ አዲስ ባትሪ ከ10% ወደ 70% ለመሙላት የወሰደበት ጊዜ 3 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ ብቻ ሲሆን፣ በ8 ደቂቃ ውስጥ ደግሞ እስከ 97% መሙላት ችሏል። ባትሪው ይህን ያህል ፈጣን ሊሆን የቻለው ባለው አዲስ የቴክኖሎጂ አሰራር ሲሆን፣ በሙከራው ወቅት ባትሪው እንዳይሞቅ እና የረጅም ጊዜ ህይወቱ እንዳይጎዳ ተደርጎ የተሰራ ነው።
ይህ አዲስ ባትሪ ለገበያ ከበቃ፣ አሁን ላይ ከ10% ወደ 70% ለመሙላት 5 ደቂቃ የሚወስደውን የBYD Blade ባትሪን የሚበልጥ ይሆናል። ምንም እንኳን ባትሪው አሁንም በሙከራ ደረጃ ላይ የሚገኝ እና ለሽያጭ የሚወጣበት ቀን ባይታወቅም፣ ወደፊት የኤሌክትሪክ መኪኖችን የመሙያ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሳጥር ይጠበቃል።
#afromekina
Loading content...
