ቡርኪናፋሶ በነዳጅ ማደያዎች የደህንነት
ካሜራዎችን አስገዳጅ አደረገች
ለሽብርተኞች የሚቀርበውን ነዳጅ ለመግታት ያለመ ነው ተብሏል
ቡርኪና ፋሶ የሽብርተኝነትን የገንዘብ ምንጭ ለመግታት፣ በነዳጅ ማደያዎች የደህንነት ካሜራዎችን አስገዳጅ ማድረጓ ተዘግቧል፡፡
የታጠቁ ቡድኖችን እንቅስቃሴ ለመስበር መንግሥት ከታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎች የቪዲዮ ክትትል ሥርዓቶችን እንዲተክሉ የሚያስገድድ አዋጅ ይፋ አድርጓል፡፡
ጥቅምት 27 የወጣ የመንግሥት አዋጅ፣ የደህንነት ካሜራ ቀረጻዎች ቢያንስ ለሁለት ወራት እንዲቀመጡ የሚያዝ ሲሆን፤ ባለሥልጣናትም ጥብቅ የሕግ ተገዢነት ፍተሻዎችን ያስፈጽማሉ ተብሏል።
የጸጥታ ሚኒስትር ማሃማዱ ሳና፤ እርምጃው ለሽብርተኞች የሚቀርበውን የነዳጅ አቅርቦት ለመቁረጥ እንዳለመ በመግለፅ፤ በዘርፉ ትብብር ቢኖርም የማጭበርበር ድርጊቶችና ቸልተኝነት የሽብርተኞች አቅርቦቶችን በተዘዋዋሪ ማመቻቸታቸውን እንደቀጠሉ መናገራቸውን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
#afromekina
Loading content...
