ረዥም ዓመታት ባስቆጠሩ ተሽከርካሪዎች "የካር ሾ" ውድድር ሊካሄድ ነው
የአዲስ አበባ ሞተር ስፖርት አሶሴሽን ’’የካር ሾው’’ና ራሊ ውድድር የፊታችን ጥር 23 እና 24 እንደሚያከናውን አስታወቀ።ውድድሪ በሁለት ዋና ዋና ቀናት ተከፍሎ የሚካሄድ ሲሆን ጥር 23 በአድዋ መታሰቢያ ይካሄዳል፡፡ ጥንታዊው በሆኑ ተሸከርካሪዎች በተለያዩ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ጉዞ ያደርጋሉ።
ከአድዋ መታሰቢያ ተነስተው በቸርችል ጎዳና፣ ቴዎድሮስ አደባባይ፣ አንድነት ፓርክ፣ ቤተመንግስት፣ ሸራተን አዲስ፣ መስቀል አደባባይ፣ ቦሌ፣ ኢምፔሪያል፣ መገናኛ፣ እንግሊዝ ኤምባሲ እና በሚኒሊክ ሆስፒታል አድርገው ጃንሜዳ ይገባሉ።በጃንሜዳ ውስጥ የመኪና ትርኢት እና የልጆች ፌስቲቫል የሚካሄድ ሲሆን ጥር 24 ቀን "ኢንዶር ራሊ ተብሎ የሚጠራው ውድድር በጃንሜዳ ውስጥ ይካሄዳል።
የፍጻሜ ውድድር እና የሽልማት ስነ-ስርዓቱ በጃንሜዳ ውስጥ በማከናወን ፌስቲቫሉ እንደሚጠናቀቅ የአዲስ አበባ የሞተር ስፖርት አሶሴሽን ምክትል ዳይሬክተር ልዑል ፀጋዬ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።ተሽከርካሪዎች ከሚነሱበት ቦታ ጀምሮ እስከ ሚደርሱበት ቦታ ድረስ የትራፊክ ባለሙያዎች የሚኖሩ ሲሆን የእሳት አደጋ እና የአንፑላንስ ተሽከርካሪዎች ይኖራሉ ተብሏል።
በመንገድ ላይ የሚደረጉ አደገኛ የመኪና እሽቅድምድሞችን ለመቀነስ፣ ወጣቶች በዝግጅቱ ላይ እንዲሳተፉና ወደ ስፖርቱ እንዲመጡ ጥረት እየተደረገ ሲሆን የድራግ ሬስ እና የጥንታዊ መኪኖች አውደ ርዕይ ተዘጋጅቷል።እስካሁን ባለው መረጃ ከ16 በላይ ተወዳዳሪዎች ተመዝግበዋል።
#afromekina
Loading content...
