የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እያሳየ ነው።
ዓለም አቀፍ የዘርፉ ዘገባዎች የነዳጅ ጭማሪ እየታየ ያለው በኢራን እና ቬንዝዌላ ባለ ውጥረት ነው ተብሏል።
በኢራን ከምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ (ከኑሮ ውድነት) ጋር በተያያዘ ሕዝባዊ ተቃውሞ ተቀስቅሶ ሁለት ሳምንት ተቆጥሯል።
ኢራናውያን ከኢኮኖሚ ቀውስ ጋር ተያይዞ በመንግሥታቸው ላይ በምሽት ሳይቀር አደባባይ እየወጡ ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ።
በነዚህ ሀገራት ያለውን ሁኔታ ተንተርሶ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ከዓለም አቀፍ ዘገባዎች መረዳት ችለናል።
አንድ በርሜል ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ 62.4 ዶላር ሲሆን ትላንት ከነበረው በ0.7% ዛሬ ጨምሯል።
በአሜሪካ ነዳጅ ገበያ እንደመለኪያ በሚታየው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዴት አንድ በርሜል ነዳጅ 58.1 ዶላር እየተሸጠ ነው። ትላንት ከነበረው በ0.6% ጭማሪ ታይቷል ዛሬ።
#afromekina
Loading content...
