የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማሟላት ተጨማሪ ከ900 በላይ አውቶብሶች እንደሚያስፈልጉ ተገለጸ
👉 በ5ዓመት ጊዜ ውስጥ 5 ሺሕ አውቶብሶች ይስፈልጋሉ ተብሏል
የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ ከሚገኙ የብዙሃን ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ 954 አውቶብሶች እንደሚያስልጉ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ለአሐዱ ራዲዮ ገልጿል፡፡
በሚኒስቴሩ የትራንስፖርት አገልግሎት እና ቁጥጥር ዘርፍ አማካሪ አቶ አሰፋ አዲስ ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማሟላት ተጨማሪ 954 አውቶብሶች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል፡፡
አክለውም፤ የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማሟላት በ5 ዓመት ጊዜ ውስጥ 5 ሺሕ አውቶብሶችን እንደሚያስፈልጉ ነው የገለጹት።
በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ አጠቃላይ የተሽከርካሪዎች ብዛት 15 ሺሕ 653 እንደሆነም አማካሪው ተናግረዋል።
እንደ እሳቸው ገለፃ፤ ከ2018 እስከ 2022 ድረስ በየዓመቱ ተጨማሪ አውቶቡሶች የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻለ በእቅድ ተይዟል።
ሕብረተሰቡን የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማቻል በተያያዘው እቅድ መሰረት፤ በ2019 ዓ.ም ከ1 ሺሕ በላይ ተሸከርካሪዎች እንዲሁም፤ በ2020 1 ሺሕ 52 ተሽከርካሪ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል መታቀዱን ገልጸዋል።
#afromekina
