ዳንጎቴ ናይጄሪያን ከዓለማቀፉ የነዳጅ
ቀውስ እንደሚታደጋት አረጋገጠ
በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የዓለምን የነዳጅ ገበያ ባናወጠበትና የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ሰማይ በነካበት በዚህ ወቅት፣ የዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ለናይጄሪያውያን የብስራት ዜና ይዞ ቀርቧል። በርካታ የዓለም አቀፍ ማጣሪያዎች በጦርነቱ ሳቢያ ስራቸውን እያቆሙ ባለበት አስቸጋሪ ወቅት፣ ግዙፉ የዳንጎቴ ፋብሪካ ለሀገር ውስጥ ገበያ ቅድሚያ በመስጠት የናይጄሪያን የነዳጅ ዋስትና ለማረጋገጥ ቃል ገብቷል።
ይህ እርምጃ ሀገሪቱን ከዓለም አቀፍ የአቅርቦት መቆራረጥ የሚታደግ "የነዳጅ ጋሻ" ተደርጎ ተወስዷል።
ፋብሪካው በዲፖ መውጫ ዋጋ ላይ ያደረገው መጠነኛ ማስተካከያ፣ ከውጭ ሀገር ነዳጅ አምጥተው ለሚያከፋፍሉ የግል ድርጅቶች የሚሰጥ ድጋፍና ለሀገራዊ ጥቅምና መስዋዕትነት ተብሎ የተደረገ መሆኑን ገልጿል።
ዳንጎቴ የሀገር ውስጥ ማጣሪያ መኖር ናይጄሪያን ከውጭ ጥገኝነት እንደሚያላቅቃትና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ የፖለቲካ ቀውሶች በናይጄሪያውያን የዕለት ተዕለት ሕይወት ላይ የሚያሳድሩትን ተፅዕኖ እንደሚቀንስ አፅንዖት ሰጥቷል። ይህ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የፈሰሰበት ፋብሪካ፣ አሁን ላይ ለአፍሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚ የህልውና ዋስትና ሆኖ ብቅ ብሏል።
አማኑኤል አክሎግ
#afromekina
