የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ከ7መቶ ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ግንባታና ጥገና ማከናወኑን ገለጸ
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ7መቶ8 ኪሎ ሜትር በላይ የግንባታና የጥገና ስራዎች ተከናውነዋል ብሏል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ 6 ወራት ውስጥ 533.34 ኪሎ ሜትር የግንባታና የጥገና ስራዎችን ለማከናወን አቅዶ እንደነበር ገልጾ፤ ከዕቅዱ በላይ ማከናወኑን አስታዉቋል፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ የዕቅድ አፈፃፀም ከ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀርም የ51.5 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ነዉ የተባለዉ፡፡
ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ከተከናወኑት አጠቃላይ 134.8 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍኑ የመንገድ ግንባታ ስራዎች መካከል 31.8 ኪሎ ሜትር የአስፋልት፣ 44.1 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ፣24 ኪሎ ሜትር የሳይክል መንገድ 25.7 ኪሎ ሜትር የኮብል ንጣፍ እና 7.9 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ ስራዎች መሆናቸዉን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ገልጿል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከግንባታ ስራዎች ጎን ለጎን በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ 66.46 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 12.5 ከ.ሜ የጠጠር፣ 198 ኪሎ ሜትር የድሬኔጅ መስመሮች ፅዳት፣ 4 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመር ዕድሳት፣ 21.3 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ጥገና እና ሌሎችንም የጥገና ስራዎችን አከናውኛለሁ ብሏል፡፡
በአማኑኤል አክሎግ
#afromekina
Loading content...
