ኤርባስ ወደ 6 ሺ የሚጠጉ A320 ሞዴል አውሮፕላኖች አጣዳፊ ጥገና እንዲያደርጉ አሳሰበ።
ከበረራ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌር ጋር በተገናኘ ችግር መግጠሙን ጠቅሶ ማሻሻያ ያስፈልጋል ያለው ግዙፉ የአውሮፓ አውሮፕላን አምራች ነው።
የአየር መንገዶች ለA320 አውሮፕላኖቻቸው አፋጣኝ ጥገና እንዲያደርጉ አሳስቧል።
ይህ ጥሪ ከበአል ወቅት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የገበያ ወራት ላይ የሚገኘው የበረራ ቢዝነስ በከፍተኛ ደረጃ የሚጎዳ እንደሆነ ተጠቅሷል።
በዚህም ወደ ግማሽ የሚጠጋ የበረራ እንቅስቃሴ ይታጎላል ነው የተባለው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤርባስ አውሮፕላን ይዞታው እየጨመረ ቢሆንም መሰል ሞዴል አውሮፕላኖችን እንደማያበር ታውቋል።
#afromekina
Loading content...
