ለአጭርም ይሁን ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍጹም የተከለከለ ነው ! " - ፖሊስ
ከዛሬ ጀምሮ የመንገድ ግንባታ በሚደረግባቸው ቦታዎች ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማትና የመንገድ ግንባታ በሚደረግባቸው ፦
1. ከቅዱስ ኡራኤል፣ በአትላስ ሆቴል ኤድሞል እስከ ቦሌ ብራስ ድረስ፣
2. አደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ
የሚቆሙ ተሽከርካሪዎች በመንገድ ስራው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደሩ መሆኑን ገልጿል።
በተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ የግንባታ ስራውን ከሚያከናውኑት ተሽከርካሪዎች በስተቀር ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪን አቁሞ መሄድ ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
#afromekina
Loading content...
