🇪🇹 ኢትዮጵያ ከ5 ዓመት በኋላ በ2030 ሀያ በመቶ ተሽከርካሪዎቿን በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ለማድረግ ማቀዷ ተገለፀ
ይህንን ዕቅድ እንዲሳካ እንደ ግብር መቀነስ የመሳሰሉ ድጋፎች እንደሚደረጉ በኢ-ሞቢሊቲ ሳምንት ላይ በተረደገ የባለሙያዎች ምክክር ላይ ተብራርቷል።
🚗🔌 የኤሌክትሪክ መኪኖች የቤት እና የሕዝብ ማጓጓዣ መኪኖችንም እንዲሚያካትቱ የተነገረ ሲሆን ቀሪዎቹም ወደ ኤሌክትሪክ እንደሚቀየሩ በጥናቱ ውስጥ ተመላክቷል።
🌱 ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ እና የአረንጓዴ ልማት ኢኮኖሚ ስትራቴጂን ቀርጻ ወደ ሥራ በመግባት ከአየር ንብረት ለውጥ ችግሮችን ራሷን ለመከላከል እየሠራች መሆኑ ተገልጿል ስትል በስፍራው የተገኘችው የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግባለች።
#afromekina
Loading content...
