የፌደራል ፖሊስ ለተሽከርካሪዎቹ የሰሌዳ ለውጥ ሊያደርግ ነው
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተሽከርካሪዎቹን የሰሌዳ ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታውቋል።
አዲሱ የሰሌዳ ሥርዓት በሕገ-ወጥ መንገድ የማይባዙና ምስጢራዊ የደኅንነት መለያዎች ያሏቸው ናቸው።
ከዘመናዊ የመረጃ ቋት ጋር የተሳሰሩ በመሆናቸው እንቅስቃሴን ለመከታተል ያስችላሉ፡፡
ማንኛውንም የዲሲፕሊን ጥሰት ለመቆጣጠርና የፖሊስን ሥነ-ምግባር ለማስከበር ይረዳሉ።
በ2030 ወደ ሙሉ ዲጂታል አሠራር ለመሸጋገር የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ትልቅ ሚና እንደሚጫወትም ተገልጿል።
አዲሱ የሰሌዳ ሥርዓት በነገው ዕለት በይፋ ይመረቃል።
#afromekina via etv
Loading content...
