42 መናኸሪያዎች ቢገነቡም የመዲናዋን ነዋሪዎችን ፍላጎት ለማሟላት ተጨማሪ የትራንስፖርት መናኸሪያ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ
በአዲስ አበባ ከተማ 42 የታክሲ እና አውቶብስ መጫኛ እና ማውረጃ የከተማ መናኸሪያ ግንባታ ቢከናወንም ከሕዝቡ ብዛት እና ፍላጎት ጋር እንዳልተመጣጠነ የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አስመሮም ብርሃነ፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የትራንስፖርት መጫኛ እና ማውረጃ ቦታዎች ፍላጎት የሚያሟሉ ግንባታዎችን በማካሄድ በከተማ መናኸሪያዎች ላይ የሚታየውን መጨናነቅ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል።
የትራንስፖርት መሰረተ ልማቱ ወደኋላ መቅረቱን ያነሱት አቶ አስመሮም፣ ምቹ የትራንስፖርት መናኸሪያ ግንባታ መከናወኑ ለከተማዋ የትራፊክ ፍሰት ከፍ ያለ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
በአጠቃላይ በከተማዋ ዕየታየ ያለውን የመናኸሪያዎች እጥረት ለመቅረፍ የተጀመሩ አዳዲስ ግንባታዎችና የመሰረተ ልማት ማሻሻያዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ተብሏል።
#afromekina
Loading content...
