በዲላ ከተማ በመኖርያ ቤት ተከማችቶ የነበረ 360 ሊትር ተቀጣጣይ ነዳጅ ቤንዚን መያዙ ተገለፀ
በህገ ወጥ መንገድ በመኖርያ ቤት ተከማችቶ የነበረ ተቀጣጣይ ነዳጅ ቤንዚን ከህብረተሰቡ በተሰጠ ጥቀማ መነሻ በፍርድ ቤት ብርበራ ትዕዛዝ መሠረት መያዙን የዲላ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኢንስፔክተር በዛብህ ማሩ ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል።
በዲላ ከተማ ሀሮ ወላቡ ክፍለ ከተማ አልቾ ቀበሌ አቶ ግዛው ዶር መኖርያ ግቢ ውስጥ 14 የሚከራይ ሰርቪስ ክፍል በአለበት ህገ ወጥ ነጋዴ የሆነው አቶ ሀብታሙ ሳል አንድ ክፍል ተከራይቶ ያለአግባብ
360 ሊትር ጀሪካን እና በሀይላንድ ቤንዚን አከማችቶ የነበረ መሆኑን ገልጸዋል።
ተቀጣጣይ ነዳጅ ቤንዚን ለማስቀመጥ ከተፈቀደ ቦታ ውጪ በህገ ወጥ መንገድ በመኖርያ ቤት ማከማቸት በሰው የሕይወት እና በንብረት ከፍተኛ ጉዳት እያሰከተለ መሆኑን እያወቁ ለግል ጥቅም ብቻ በማሰብ የምደረግ የንግድ ስርዓት ልውውጥ ላይ በተሰማሩ ግለሰቦች የወንጀል ምርመራ በማጣራት ህጋዊ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ እናደርጋለን ሲሉ ገልጸዋል ።
ተቀጣጣይ ነዳጅ ከተፈቀደ ቦታ ውጭ ማከማቸትም ሆነ ማስቀመጥ አደጋ እያስከተለ በመሆኑ የአካባቢው ህብረተሰብ የተለመደውን ጥቆማ እና መረጃ ለፖሊስ በማሳወቅ እና በዚህ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል።
#afromekina
Loading content...
