የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ናይጄሪያ ሳምንታዊ የበረራ ቁጥሩን ወደ 34 በማድረስ ቀዳሚ አየር መንገድ ሆነ
የኢትዮጵያ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ናይጄሪያ የሚያደርገውን ሳምንታዊ የበረራ ቁጥር ወደ 34 አሳድጓል። ይህም አየር መንገዱን ወደ ናይጄሪያ በብዛት የሚበር አየር መንገድ አድርጎታል።
አየር መንገዱ በዚህ ሳምንት አዲስ በረራ ወደ አቡጃ ሲጀምር የአየር መንገዱ የናይጄሪያ ቀጣና ማኔጀር ፍሬህይወት መኮንን አየር መንገዱ አዲስ በረራ ብቻ ሳይሆን የጀመረው በኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ መካከል ያለውን ግንኙነት ያጠናከረ ነው ብለዋል።
አየር መንገዱ በዚህ ሳምንት ወደ ሌጎሱ ናማዲ አዚኪዌ አየር ማረፊያ ተጨማሪ 3 በረራዎችን ጀምሯል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ናይጄሪያ ከ65 ዓመታት በፊት በረራ የጀመረ ሲሆን ናይጄሪያን ከ150 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ጋርም አገናኝቷል።
አየር መንገዱ በአሁኑ ጊዜ 14 ሳምንታዊ በረራዎችን ወደ ሌጎስ፣ 10 ወደ አቡጃ እንደዚሁም አምስት አምስት ጊዜ ደግሞ ወደ ካኖ እና ኢኑጉ እየበረረ ይገኛል።
#afromekina
Loading content...
