በኢትዮጵያ-ጅቡቲ ባቡር ለመጀመሪያ ጊዜ የነዳጅ ትራንስፖርት ሙከራ በስኬት ተከናወነ
ኢትዮጵያ 120,000 ሊትር ነዳጅ በባቡር በማጓጓዝ፣ በሀገሪቱ የሎጂስቲክስና የኢነርጂ ዘርፍ ትልቅ ስኬት የታየበትን የመጀመሪያውን የሙከራ ጉዞ አጠናቃለች።
ይህ የሙከራ ጉዞ የተከናወነው በኢትዮጵያ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ሲሆን፣ ለዓመታት አገልግሎት ሳይሰጡ ቆይተው የነበሩ ለነዳጅ ማጓጓዣ ተብለው የተሰሩ ልዩ የባቡር ታንከሮችን (Wagons) በመጠቀም ነው።
ይህ እርምጃ የሀገሪቱን የሎጂስቲክስ ስርዓት ለማዘመን፣ የትራንስፖርት ወጪን ለመቀነስና በከባድ የነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለማቃለል መንግስት እየወሰደ ካለው ሰፊ ስትራቴጂያዊ ጥረት ውስጥ አንዱ አካል ነው።
#afromekina
Loading content...
