በአዲስ አበባ 32 የቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች አገልግሎት ሊጀምሩ ነው
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመላ ሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን እየገነባ መሆኑን አስታውቋል።
ተቋሙ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ የሦስት ጣቢያዎችን ግንባታ አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ያደረገ ሲሆን፣ በቀጣይም ተጨማሪ 34 ፕሮጀክቶችን ለማስጀመር አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ከ140 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቢኖሩም፣ የቻርጅ ማድረጊያ መሠረተ ልማት እጥረት ትልቅ ፈተና ሆኖ ቆይቷል።
ይህንን ችግር ለመቅረፍ ተቋሙ በመጀመሪያው ምዕራፍ በአዲስ አበባ 32፣ በሌሎች የክልል ከተሞች ደግሞ 8 በድምሩ 40 የቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን ለመገንባት ርብርብ እያደረገ ይገኛል።
#afromekina
Loading content...
