ቢ ዋይ ዲ በተሽከርካሪ ሽያጭ ቴስላን ሊቀድም ነው ተባለ
የቻይናው ተሽከርካሪ አምራች ቢ ዋይ ዲ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ የኤለን መስኩን ቴስላ ኩባንያ በመብለጥ ቀዳሚው ሻጭ ሊሆን ነው።
ኩባንያው እንደገለጸው ዓመታዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽያጩ በ28 በመቶ አድጎ 2 ነጥብ 25 ሚሊየን ደርሷል።
ዓመታዊ ሽያጩን ገና ይፋ ያላደረገው የቴስላ ኩባንያ 1 ነጥብ 65 ሚሊየን ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ሊኖረው እንደሚችል ባለሙያዎች ተንብየዋል።
ቴስላ ከባለቤቱ ኤለን መስክ ፖለቲካዊ ተሳትፎና ከቻይና ተሽከርካሪ አምራቾች የሚገጥመው ፉክክር ከባድ ዓመት እንዲያሳልፍ እንዳስገደደው ቢቢሲ አስነብቧል።
#afromekina
Loading content...
