ጃፓን የሩሲያን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ አለመግዛት እንደማትችል ገለጸች
9 በመቶ ያህል ፍላጎቷን የምታሟላው ከሩሲያ ነው
የሩሲያ ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ምርቶች ወደ ሀገር እንዳይገቡ እገዳ መጣል ለቶኪዮ ፈታኝ ነው ሲሉ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናኤ ታካይቺ ማክሰኞ ዕለት ከአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ባደረጉት ውይይት መናገራቸውን የጃፓን መንግሥት ምንጮች ለስፑትኒክ ገልፀዋል።
እንደ ምንጮቹ ገለጻ፤ ታካይቺ የሩሲያ ጋዝ በድንገት ወደ ጃፓን እንዳይገባ ማገድ፣ በሀገሪቱ የኃይል አቅርቦትና ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል አሳስበዋል።
“ጃፓን ከእነዚህ ፕሮጀክቶች ብትወጣ፤ ሩሲያና ቻይና ብቻ ናቸው ተጠቃሚ የሚሆኑት” ሲሉ ታካይቺ ተናግረዋል።
አሜሪካ የቡድን ሰባት ሀገራት የሩሲያ የኃይል ምንጮችን ሙሉ በሙሉ መግዛት እንዲያቆሙ እያሳሰበች ትገኛለች። የአውሮፓ ህብረት የሩሲያ ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ምርቶች ግዢ ላይ ሙሉ እገዳ ለመጣል ከወዲሁ እያጤነ ነው። ሆኖም ጃፓን ከፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፍላጎቷ ውስጥ 9 በመቶ ያህሉን የምታሟላው ከሩሲያ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
#afromekina
Loading content...
