ባለስልጣኑ ሁሉም ነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች በአንድ ማኅበር እንዲደራጁ ሊደረግ ነው አለ
የነዳጅ አቅራቢነት ፈቃድ አግኝተው በሥራ ላይ ያሉ ሁሉም ነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች በአንድ ማኅበር እንዲደራጁ ሊደረግ መሆኑን የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን አስታውቋል።
ይህም በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በወጥነት ለመቆጣጠር ያስችል ዘንድ መሆኑን ገልጿል።
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከሚገኙ ነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች ውስጥ የነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች ማኅበር አባል የሆኑት ሰባት ብቻ መሆናቸውን ለሪፖርተር የገለጹት የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ደስታው መኳንንት ከእነዚህ ኩባንያዎች ጋር ብቻ መሥራት ውጤታማ እማያደርግ ነው ብሏል።
ለዚህም ሲባል ማንኛውም በነዳጅ አቅራቢነት ፈቃድ አግኝቶ እየሠራ ያለ ኩባንያን፣ በአስገዳጅነት የነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች ማኅበር አባል እንዲሆን የሚደነግግ ረቂቅ ደንብ እየተዘጋጀ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
#afromekina
Loading content...
