" ጠንከር ያለ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል " - ፖሊስ
ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው በተሽከርካሪ መስታወት ላይ ፦
- ጥቁር ስቲከር የሚለጥፉ፣
- የአደጋ ጊዜ መብራቶችን የገጠሙ፣
- ጥቁር መስታወት ያስገጠሙ
- ለአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎች የተፈቀዱ ጡሩምባዎችና መብራቶችን በገጠሙ አሸከርካሪዎች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳሰበ።
ባለፈው ስድስት ወር በተደረገ ቁጥጥር 33 ሺህ 059 አሽከርካሪዎች ምንም አይነት ፈቃድ ሳይኖራቸው በተሽከርካሪያቸው መስታወት ላይ ጥቁር ስቲከር ባደረጉ እንዲሁም በተደመሰሰ እና በተፋፋቀ ሰሌዳ ሲያሽከረክሩ በተገኙ 15 ሺህ አሸከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል፡፡
በቁጥጥሩ ወቅት ጥቁር ስቲከር ከማድረግ ባለፈ ጥቁር መስታወት ባደረጉ እና የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎችን የሚጠቀሙበትን የአደጋ ጊዜ ጥሩባ ባስገጠሙ ህገ-ወጦች ላይ እርምጃ እንደተወሰደባቸው አስታውቋል፡፡
" በተሽከርካሪ መስታዎት ላይ የሚለጠፍ ስቲከር አሽከርካሪው የውጪውን እንቅስቃሴ በትክክል ተመልክቶ እንዳያሽከረክር እንዲሁም የትራፊክ ተቆጣጣሪዎችም በተሽከርካሪ ውስጥ ያለውን ሁኔታ እንዳይቆጣጠሩ እንቅፋት እየፈጠረ ነው " ያለው ፖሊስ ከዚህም በላይ አንዳንድ ወንጀል ፈፃሚዎች ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ወንጀል ሲፈፅሙ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውንና ጉዳዩ አሳሳቢ እንደሆነ አመልክቷል።
" ከሚመለከተው የጸጥታ፣ ደህንነትና የትራንስፖርት ተቋማት ምንም ዓይነት ፈቃድ ሳይኖራቸው በተሽከርካሪ መስታወት ላይ ጥቁር ስቲከር ያደረጉ፣ ጥቁር መስታወት ያስገጠሙ እንዲሁም ከአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎች ጋር የሚመሳሰል ጥሩምባ እና መብራት እየተጠቀሙ ያሉ ባለ ንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች ላይ ጠንከር ያለ ህጋዊ ርምጃ ይወሰዳል " ሲል አስጠንቅቋል።
#afromekina
Loading content...
