" ከአውሮፕላን ነዳጅ በቀር የሌሎች ነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል " - ንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
የቤንዚን፣ የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲን፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር ሲሸጥበት በነበረው እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስቀመጠው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ከጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል።
ከአውሮፕላን ነዳጅ የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ በጥር በነበረበት ይቀጥላል ተብሏልም
የአውሮፕላን ነዳጅ የችርቻሮ መሽጫ ዋጋ በአዲስ አበባ ከተማ 136.80 ብር/በሊትር እንዲሆን በመንግሥት መወሰኑንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።
፦ አሁን ላይ ያለው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ስንት ነው ?
- ቤንዚን 129.12 ብር በሊትር
- ነጭ ናፍጣ 129.12 ብር በሊትር
- ኬሮሲን 129.12 ብር በሊትር
#afromekina
Loading content...
