የዓለም የነዳጅ ገበያ ከፍተኛ መናወጥ ሊገጥመው እንደሚችል ተሰጋ
ዛሬ በመካከለኛው ምስራቅ በነገሰው ግጭት ምክንያት የነዳጅ ዋጋ በአንድ በርሜል ከ100 ዶላር በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ተተንብዮአል።
ኢራን ለአጥቂዎቹ በሰነዘረችው የአጸፋ ሚሳይል ምላሽ ሳቢያ ውጥረቱ የከረረ ሲሆን፣ በተለይም በሆርሙዝ የጠባብ ባህር መስመር ላይ ሊደቀን የሚችለው የእንቅስቃሴ መዘጋት ለዋጋው መናር ዋነኛ ምክንያት እንደሚሆን ተገልጿል።
ይህ ስትራቴጂካዊ የባህር መስመር የዓለምን ሩብ ያህል የነዳጅ ንግድ የሚያስተናግድ በመሆኑ፣ መስተጓጎል ቢፈጠር ዋጋው እስከ 150 ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ተንታኞች አስታውቀዋል።
ይህም በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ሊያስከትል ይችላል ተብሎ ተፈርቷል።
በአማኑኤል አክሎግ
#afromekina
Loading content...
