በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በተደረገ ክትትል ህገወጥ የነዳጅ ምርት ተገኘ‼️
በአፋር ክልል ሎጊያ ከተማ የነዳጅ ምርት ቅሸባ ይፈጸምበታል የተባለ ቦታ በክትትል መገኘቱ ተገለጸ።
በትላንትናው ዕለት በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር የነዳጅ ምርቶች ላይ ቅሸባ የሚፈጸምበት ሥፋራ ላይ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በተደረገ ክትትል ወንጀሉን ሲፈጽሙ የተገኙ አካላት በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል፡፡
በሎጊያ ከተማ ውስጥ የተገኘው አስራ ሶስት(13) የሳጠራ ቤትና መጠለያ ሲሆን በዕለቱም ነዳጅን በሕገ-ወጥ መንግድ በመቀሸብ ላይ የተገኘ አንድ የነዳጅ ጫኝ ተሸከርካሪ ቦቴ እና ከተሸከርካሪው ላይ ነዳጅ በመቀነስ ሲሸጡና ሲገዙ በተገኙ አስር ግለሰቦች ተይዘዋል።
በግምት ከሁለት መቶ(200) በላይ የነዳጅ ምርት የያዙ በርሜሎች በየክፍሎቹ እንደሚገኙ መረጃው ጠቅሶ የሚመለከተው አካል ግምታዊ ዋጋ ሲያወጣላቸው እንደሚገለጽ ከነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
#afromekina
Loading content...
